Current Articles | Categories | Search | Syndication
ጌታን ከማወቃችን በፊት በበደላችንና በኃጢአታችን ምክንያት መንፈሳችን ሙት ነበር (ኤፌሶን 2፣1)። ጌታን ካገኘን በኋላ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ውስጣችን ገብቶ አዲስ ሕይወትን ሰጠን፣ በመንፈስም ሕያዋን ሆንን (ሮሜ 8፣10-11)፤ ያን ጊዜ መንፈሳዊ ዓይናችን ተከፈተ፣ ያኔም ማን መሆናችን ብቻ ሳይሆን የማን መሆናችንን ተረዳን።
"ለበረከትም ሁን! You Shall Be a Blessing!"
በ1998 ዓ.ም. ግንቦት ወር ውስጥ Rev. Ruddy Wiebe ከተባሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ፕሪንሲፓልና ሌሎች 6 ከተለያዩ አገሮች የመጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ጋር ፔንሲልቫንያና ኒውዮርክ ለአንድ ሳምንት በመዘዋወር በተለያዩ የአሜሪካ አብያተ ክርስቲያን የማገልገልና የመገልገል ዕድል ገጥሞን ነበር።