Register
|
Login
Home
About
Our Vision
Our History
Pastors
News and Events
News
Reading Articles
Sunday School
Events (Calendar)
Community
Bible Study Locations
Social Needs
Resources and Bookstore
Contact Us
Donate
Article Categories
Bible Study (1)
Devotionals (2)
Evangelism and Mission (1)
Family Matters (2)
General (3)
Reading Articles
Current Articles
|
Categories
|
Search
|
Syndication
Tuesday, January 22, 2008
ስለቤተስብ አመጣጥና ጉዞ
By mnegusse @ 5:10 PM :: 2572 Views ::
2
Comments
::
::
Family Matters
ስለቤተስብ አመጣጥና ጉዞ
በዚህ በመጨረሻው ዘመን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በክብሩ ዳግም ተመልሶ ለመምጣት በደጅ በሆነበት በአሁኑ ወቅት በእርሱ
ቸርነትና ምህረት
ሁላችንንም በቤተስብ ለዚህ ዘመን ስላደረስን ለታማኙ አመላካችን ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁንለት።
የወንጌል ተልዕኮ በአሐዛብ መካከል በይበልጥ እንዲስፋና በወገኖቻችንም መካከል የጌታችንና
የመድ
ኃኒ
ታችን የመንግሥት ወንጌል በሚገባ እንዲስበክ የክርስቶስ አካል የሆነችውን
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤት ክርስቲያን በቶሮንቶ ከተማ
በጌቻችን ፈቃድ ተመስርታልናለች። ይህች ቤተክርስቲያን ከምትሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል አንዱ የሆነው የቤተስብ አገልግሎት ክፍል ነው።
ባለንበት ዘመን በመላው የአለም ሕብረተስብ ስዉንና ቤተስቡን የሚያናውጡ ጉልህ የሆኑ የቤተስብ ችግሮች እንዳሉ ግልጽ ነው። በተለይም እኛ በውጭ አገር የምንገኝ ከኢትዮጵያ ህብረተስብ ሀገራችንን የተውንበት በመገፋት እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶችም ናቸው፤ አሁንም በመጻተኛነት በዚህ በምንኖርበት ምድር ባህሉ አዲስ በመሆኑ ምክንያት የመጣንበትን የቤተስብ አመራር ባህልና ያለንበትን ለማስታረቅ ጥረት በማደረግ ላይ እንገኛለን። አንዳንዴም ውጤቱ ሳያምር ይቀርና አንዳንዶች ቤተስቦች ከሁለቱም ሳይሆኑ ለአገሩ ባዳ ለስውም እንግዳ ሆነው ይታያሉ። ይህንንና የመሳስልሱትን የቤተስብ ችግሮች ለመርዳት በቶሮንቶ ከተማ የምትገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ወገኖችን በይበልጥ ለመደገፍና ለመምክር የቤተስብ አገልጋይ በመጋቢ ደረጃ አሰማርታለች።
በተለያዩ ጠቢባን በየዘመናቱ በሚደረጉት የፈጠራ ውጤቶች ወይም ዕቃዎች የራሳችው ፈጣሪ አላቸው። ለምሳሌ ያህል ባነሳው በዘመናችን በአየር ላይ የምንጓዝበት አውሮፕላን በዚህ መልኩ ከመቅረቡ በፊት የበረራ የመጀመሪያው ጽንስ ሃሳብ የመነጨውና የመጀመሪያው የሙከራ አውሮፕላን የተስራው ከራይት ብራዘርስ ከተባሉት ወንድማማቾች አንደነበረ ከአቪዬሽን ታሪክ መረዳት ይቻላል። እንደዚሁም ሌሎች እንደመብራት መኪና ኮምፒውተርና ሌሎቹም የቴክኖሎጂ ግኝቶች ሁሉ ፈጣሪ አንዳላቸው ግልጽ ነው።
የቤተስብ ፈጣሪ ወይም መስራች የሆነው ስው ሳይሆን ታላቁና የተፈራው ሕያው እግዚአብሔር እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ከዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ እንደምንረዳው እግዚአብሔር ምድርን ስማይንና ባሐርን በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ ይሁኑ ብሎ ፈጠራቸው። ስውን ከመፍጠሩ በፊት ግን ጊዜ ወስደ ለማንም ፍጥረታቱ ያላደረገውን ትኩረት በመስጠት በእራሱ መልክና ምሳሌ ስውን ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው (ዘፍ 2፡27 እና ዘፍ.2፡21-22)። ይህ የእግዚአብሔር አስራር በዘመናት ውስጥ ለትዳር ጠንቆችና ችግሮች ምክንያቶች በመሆን የቆዩትን የወንድና የሴት ጥያቄዎች በቂ መልሶችን ለመስጠት ብቃትን አስገኝቶልናል ብል ስህተት አይደለም።
እግዚአብሔር ቤተስብን ለራሱ ክብርና ለበረከት ማለትም ምድርንም በስዎች ለመሙላት ምክንያት ፈጠረ
። ለዚሁ ምክንያት ውብ ሆኖ የተፈጠረው ቤተስብ እንደዛው አልቀረም። በ
ኃ
ጢያት ጣልቃ መግባት ብዙ ነገሩን እንዳበላሽ መረዳት አስፈላጊ ይሆናል።
ከአዳም ውድቀት ጀምሮ ቤተስብ በአምላኩና በእርሱ መካከል የተስራውን የ
ኃ
ጢአትና የጥል ግድግዳ ለማፍረስ አቅም አላገኘም ከዚህም የተነሳ ውድቀቱ እየቀጠለና ጥልቅ እየሆነ ሄደ። ይህንንም ውድቀት የተመልከተ እግዚአብሔር ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ በአንድ ልጁ በጌቻችን በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሥራ ጠላት የነበሩትን ቤተስብ እርቅ ከራሱ ጋር ለማምጣት አሁንም እጆቹን ዘርግቶ ቤተስቦችን በመጠገን ተሃድሶን ለማምጣት ዝግጁ እንደሆነ ግልጽ ነው። ከዚህም ጥሪ የተነሳ ከእግዚአብሔር ዘንድ ልዩ የሆነ ፍቅርና ዕቅድ እንዲሁም አመራር ተደርጎለት እናያለን።
በዚህም አመራር እስከ ኖህ ዘመን ድረስ የነበረው የስው ዘር እግዚአብሔርን በማሳዘን በው
ኃ
ጥፋት ከምድር ላይ ጨርሶ ሲወገድ የርስቱ ቅሬታ አድርጎ በምድር ላይ ያስቀረው የኖህን ቤተስብ ነበር። በአንድ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ታዛዥ በሆነ በኖህ ቤተስብ ምክንያት ከዚያን ጊዜ አንስቶ እግዚአብሔር የቀሩትን ቤተስብ በመልካም ወንዶችና ሴቶች ሕጻናት አድገውም ወጣቶች ጎልማሶች ሽምግለውም በሆኑ ምድርን እንደገና ባረከ። ከእነዚሁም ቤተሰቦች የውጡት በመቀጠል ተባዛተው መልስው የመልካም ዜጎችና የአለም ሕብረተስብ ለመሆን በቅተው በአሁኑ ጊዜ ከ 6.5 እስከ 7 ቢልየን ሕዝብ ምንጭና መስረት ሆነው እስካለንበት ጊዜ ደረሱ። በአጠቃላይ ቤተስብ ለምድር በረከት ምክንያት እንደነበረ አሁንም እንደሆነ ግልጽ ነው።
ከላይ እንደተጠቀስው ምድር በው
ኃ
ከተዋጠች በኋላ የመጀመሪያው ቅሬታ በመሆን በእግዚአብ ሔር ጽኑ ቃልኪዳን የተቀበለው ቤተስብ ብቻ ነው። በገነት ለአዳም ከገባው ቃልኪዳን ሌላ እግዚአብሔር ቃልኪዳን ያቆመለትና ወራሽ ያደረገው ቤተስብን ነው፤ እግዚአብሔር ለኖሕና ለቤተስቡ ሲናገር “እኔም እነሆ ቃል ኪዳኔን ከእናንተና በ
ኃላ
ከሚመጣው ዘራችሁ ጋር አቆማለሁ” (ዘፍ. 9፡8-11)፤ ብሎ ተናገረ። ይህም ቃልኪዳን ተጠብቆ በእምነት አባታችን በሆነ በአብረሃም ዘር በክርስቶስ ለሁላችንም ደርሶናል። ከዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር አስቀድሞ እንደተፈጠረው እውነተኞች ቤተስብ መስራቾች በእግዚአብሔር እውቀትና ፍርሃት ውስጥ እራሳቸውን በማስገዛት የሚመላለሱ ቅዱሳን ብቻ ናቸው።
ቤተስብ በእግዚአብሔር ከተፈጠረ በኋላ በዘመናት ውስጥ የገጠሙትን ተጋድሮቶችንና ችግሮች ለመቋቋምና ጨርሶም ለማስወገድ ያልቻለባቸው ምክናያቶች አሉ። በተለያየ መልክ የሚከስቱትን ችግሮች ለማስወገድ የማይቻልበት ጊዜ አለ፤ ይሁን እንጂ ባልና ሚስት ችግሮቻቸውን በማቃለልና በመቻቻል ተግባብተው አብሮ በስላም በመኖር በአደራ ከእግዚአብሔር ለተስጡዋቸው ሕጻናቶቻቸው ቤቶቻቸውን ምቹ
የመኖሪያ አካባቢ ማመቻቸት ምርጫቸው ማድረግ ይችላሉ።
በቤተክርስቲያናችን የቤተሰብ አገልግሎት ክፍል የሚሰጡ ፕሮግራሞች፣
1. ለወጣት ምክር (Youth Counseling)
2. ቅድመ ጋብቻ ትምህርት(Premarital)
3. የጋብቻ ምክር(Marriage Counseling) 4. የቤተሰብ ምክር(Family Counseling)
5. የቁዘማ ምክር(Depression Counseling) 6. የባልና ሚስት(Relationship Counseing
7. የቤተሰብ ጥል (Crisis Counseling)
በሚቀጥለው ጠቃሚ ምክር
እስ
ከምንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑ።
የቤተስብ አግልግሎት ክፍል
Rating
1
2
3
4
5
Comments
By East @ Tuesday, April 22, 2008 6:38 PM
It is very usful counsling, I learned something which family is made by the Almight God and I have a responsblity to walk in line with the will of God in the family. God Bless you.
By
replica watches uk
@ Friday, November 25, 2011 1:40 AM
Instead of having to face the crowds and aggressive shoppers, you can get all your shopping done at home, and in much less time.
Click
here
to post a comment