Current Articles | Categories | Search | Syndication
ሦሰት ጉልቻ የተለያዩ ባሕሎችና ቋንቋዎች ጋብቻን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው የየራሳቸው የሆኑ ዘይቤዎች አሏቸው። “ሦስት ጉልቻ” ደግሞ አበው ከተመክሮ በቀሰሙት፣ ጋብቻን ለመግለጽ የተጠቀሙት የራሳችን ዘይቤ ነው። ጋብቻን በዚህ አባባል ለመግለጽ ሲሞከር ትዳር ከሁለት ሰዎች ጥምረት ባሻገር ሊስተዋል የሚገባው እውነታ እንዳለው ይታያል። አባባሉ አባቶቻችን በተመክሮ ጋብቻ ከታጋቢዎቹ ሁለትነት የዘለለ ገጽታ እንዳለው መረዳታቸውን የሚመሰክር ነው። ባደግንበት ባሕል ክልል ተወስነን ለምንኖረውም ሆነ የባህሉን ድንበርን ክልል አለፈን፣ በረሃውን አቋርጠን፣ ባሕሩን ተሻግረን ለምንኖረው ሁሉ ይህን አባባል በተመለከተ ለማሰተላለፍ የምንፈልገው መልእክት አለን። አማኞች በትዳራቸው ጸንተው አምላካቸውን የሚያሰከብር የትዳር ኑሮ መምራት እንዲችሉ ማስተማር፣ መምከርና ማበረታታት አንዱ የቤተ ከርስቲያን ተልዕኮ ነው። የሦሰት ጉልቻ ዋና አሳብም ባልና ሚስት መልካም ትዳር ለመምራት እግዚአብሔርን በሦሰተኛነት ወደ ኑሮአቸው ሊጋብዙት እንደሚያሰፈልጋቸው መጠቆም ነው። ከሁሉ በፊት “ትዳር ከየት መጣ? የትዳርስ ፈጣሪ ማን ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሣትና መልሶችን መስጠት እጅግ አስፈላጊ ነው። በዚህ ዓለም ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሁሉ ሠሪ እንዳላቸው ሁሉ፡ በወንድና በሴት መካከል ያለው ትዳርም ፈጣሪ ወይም ሠሪ አለው። እርሱም ሰማይን፡ ምድርንና ባሕርን በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ አምላካችን እግዚአብሔር ነው። “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” በማለት ከትዳር በፊት እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክና ምሳሌ እንደ ፈጠረ የእግዚአብሔር ቃል ያስተምረናል። ዘፍጥረት 1፡26-27 “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” ይላል። ቀጥሎም “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ወይም እንደ እርሱ ያለ ረዳት እንፍጠርለት” (ዘፍጥረት 2፡18፣21) በማለት ጌታ እግዚአብሔር ጋብቻን ለሰው ብቸኝነት መፍትሔ አድርጎ እንደፈጠረ ከቅዱስ ቃሉ እንማራለን። የእግዚአብሔር አሳብ ይህ ሆኖ ሳለ የሰው ልጅ በአሁኑ ሰዓት የሚገኘው ግን ባለትዳሮች በበርካታ ችግሮች ውስጥ በሚያልፉበት ዘመን ነው። ከዚህም የተነሣ ትዳርን ማፍረስና ቤተሰብን መበተን ለብዙዎች የማያዳግት ምርጫ ሆኗል። በአንድ ወላጅ ብቻ የሚያድጉ ሕፃናት የዚህ ችግር ሰለባ ሆነዋል። ጋብቻ ጣዕም ያለው እንዲሆን ባልና ሚሰት ከሁሉ በተቀዳሚ እግዚአብሔርን በሦስተኛነት ወደ ትዳራቸው ማስገባታቸው አማራጭ ሳይሆን አሰፈላጊ ነው። የትዳር ፈጣሪ የሆነው እግዚአብሔር ቅዱሰ ትዳርን የሚመራበት ግሩም የሆነ የመመሪያ ቃል አለውና! ያለዚያ ትዳር ፍሬ የሌለው የአፈርና የአጥንት ኅብረት ብቻ ይሆንና ሦሰት ጉልቻ ትርጉም የለሸ ኑሮ ይሆናል። ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የጋብቻ አገልግሎት።
ሦሰት ጉልቻ
የተለያዩ ባሕሎችና ቋንቋዎች ጋብቻን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው የየራሳቸው የሆኑ ዘይቤዎች አሏቸው። “ሦስት ጉልቻ” ደግሞ አበው ከተመክሮ በቀሰሙት፣ ጋብቻን ለመግለጽ የተጠቀሙት የራሳችን ዘይቤ ነው። ጋብቻን በዚህ አባባል ለመግለጽ ሲሞከር ትዳር ከሁለት ሰዎች ጥምረት ባሻገር ሊስተዋል የሚገባው እውነታ እንዳለው ይታያል። አባባሉ አባቶቻችን በተመክሮ ጋብቻ ከታጋቢዎቹ ሁለትነት የዘለለ ገጽታ እንዳለው መረዳታቸውን የሚመሰክር ነው።
ባደግንበት ባሕል ክልል ተወስነን ለምንኖረውም ሆነ የባህሉን ድንበርን ክልል አለፈን፣ በረሃውን አቋርጠን፣ ባሕሩን ተሻግረን ለምንኖረው ሁሉ ይህን አባባል በተመለከተ ለማሰተላለፍ የምንፈልገው መልእክት አለን። አማኞች በትዳራቸው ጸንተው አምላካቸውን የሚያሰከብር የትዳር ኑሮ መምራት እንዲችሉ ማስተማር፣ መምከርና ማበረታታት አንዱ የቤተ ከርስቲያን ተልዕኮ ነው። የሦሰት ጉልቻ ዋና አሳብም ባልና ሚስት መልካም ትዳር ለመምራት እግዚአብሔርን በሦሰተኛነት ወደ ኑሮአቸው ሊጋብዙት እንደሚያሰፈልጋቸው መጠቆም ነው።
ከሁሉ በፊት “ትዳር ከየት መጣ? የትዳርስ ፈጣሪ ማን ነው?” የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሣትና መልሶችን መስጠት እጅግ አስፈላጊ ነው። በዚህ ዓለም ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሁሉ ሠሪ እንዳላቸው ሁሉ፡ በወንድና በሴት መካከል ያለው ትዳርም ፈጣሪ ወይም ሠሪ አለው። እርሱም ሰማይን፡ ምድርንና ባሕርን በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ አምላካችን እግዚአብሔር ነው።
“ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” በማለት ከትዳር በፊት እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክና ምሳሌ እንደ ፈጠረ የእግዚአብሔር ቃል ያስተምረናል። ዘፍጥረት 1፡26-27 “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” ይላል። ቀጥሎም “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ወይም እንደ እርሱ ያለ ረዳት እንፍጠርለት” (ዘፍጥረት 2፡18፣21) በማለት ጌታ እግዚአብሔር ጋብቻን ለሰው ብቸኝነት መፍትሔ አድርጎ እንደፈጠረ ከቅዱስ ቃሉ እንማራለን።
የእግዚአብሔር አሳብ ይህ ሆኖ ሳለ የሰው ልጅ በአሁኑ ሰዓት የሚገኘው ግን ባለትዳሮች በበርካታ ችግሮች ውስጥ በሚያልፉበት ዘመን ነው። ከዚህም የተነሣ ትዳርን ማፍረስና ቤተሰብን መበተን ለብዙዎች የማያዳግት ምርጫ ሆኗል። በአንድ ወላጅ ብቻ የሚያድጉ ሕፃናት የዚህ ችግር ሰለባ ሆነዋል።
ጋብቻ ጣዕም ያለው እንዲሆን ባልና ሚሰት ከሁሉ በተቀዳሚ እግዚአብሔርን በሦስተኛነት ወደ ትዳራቸው ማስገባታቸው አማራጭ ሳይሆን አሰፈላጊ ነው። የትዳር ፈጣሪ የሆነው እግዚአብሔር ቅዱሰ ትዳርን የሚመራበት ግሩም የሆነ የመመሪያ ቃል አለውና! ያለዚያ ትዳር ፍሬ የሌለው የአፈርና የአጥንት ኅብረት ብቻ ይሆንና ሦሰት ጉልቻ ትርጉም የለሸ ኑሮ ይሆናል። ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የጋብቻ አገልግሎት።